ምዕራፍ ፩:- የዜጎች ተሳትፎ፣ ፖለቲካዊ ተሳትፎ እና የምርጫ ሥርዓቶች

Instructor
CECOE
134 Students enrolled
0
0 reviews
  • Description
  • Curriculum
  • Reviews
2.jpg

ዓላማ 

ይህ ምዕራፍ «ተሳትፎ» የሚለውን ጽንሰ-ሀሳብ ከተለመደው ትርጓሜ ባሻገር፣ በመንግሥትና በዜጎች መካከል ያለውን የሥልጣን ግንኙነት መገለጫ አድርጎ ያብራራል። በዚህም የዜጎች ተሳትፎ «ንቁ ዜግነትን» መለኪያነት ብቻ የሚገደብ ሳይሆን፣ ዴሞክራሲያዊ ቅቡልነት የሚረጋገጥበት መሠረታዊ መሣሪያ መሆኑን ያስገነዝባል።  

ይህ ምዕራፍ «ተሳትፎ» ማለት ዜጎች ንቁ መሆናቸውን ማሳያ ብቻ ሳይሆን፣ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን የሥልጣን ግንኙነት የሚገልጽና እውነተኛ ዴሞክራሲን የሚያረጋግጥ መሠረታዊ መሣሪያ መሆኑን ያስረዳል።

1) ጽንሰ-ሀሳብን የመረዳት ብቃት  ይሄውም «ሕዝባዊ ተሳትፎ»ን (ለማኅበረሰብ በጎ መሥራትን) ከ«ፖለቲካዊ ተሳትፎ» (በመንግሥትና በሥልጣን ላይ ተጽዕኖ ማሳደርን) መለየት እንዲሁም ሁለቱም በማኅበራዊ ካፒታል (በሰዎች ትስስር) እና በዜጎች በጎ ፈቃደኝነት ንድፈ-ሀሳቦች ውስጥ ያላቸውን ቦታና ሚና መግለጽ መቻል ነው።

2) የመዋቅር ትንተና ብቃት  የመዋቅር ትንተና ብቃት ማለት አንዳንድ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከሌሎች በበለጠ ለምን በስፋት እንደሚሳተፉና ይህ «የተሳትፎ ክፍተት» ከሰዎች የኑሮ ደረጃ፣ ከገቢያቸውና ከተማሯቸው የትምህርት ደረጃ (ከማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ሁኔታቸው) ጋር እንዴት እንደሚገናኝ መተንተን መቻል ነው።

3) የንጽጽር ብቃት  የንጽጽር ብቃት ማለት በዓለም ላይ ያሉ ዋና ዋና የምርጫ ሥርዓቶችን (አብላጫ ድምፅ፣ ተመጣጣኝ ውክልና እና ቅይጥ ሥርዓትን) በፍትሐዊነትና በሀገር መረጋጋት ረገድ ማወዳደር፤ እንዲሁም እያንዳንዱ የምርጫ ሥርዓት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ቁጥርና ጥንካሬ  እንዴት እንደሚወስን አስቀድሞ መገመት መቻል ነው።

4) የምርጫ ሥርዓትን ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የማዛመድ ብቃት   

 ኢትዮጵያ የምትከተለው የአብላጫ ድምፅ የምርጫ ሥርዓት፣ ብዙ ብሔረሰቦች ባሉበት የፌዴራል መዋቅር ውስጥ የሚያመጣቸውን የውክልና ጥቅሞችና የሚቀሰቅሳቸውን መዋቅራዊ ግጭቶች በማስረጃ አስደግፎ የማሳመን ብቃት ነው። 

የመዋቅር ግጭት ነጥብ፦ የዚህ ምዕራፍ ትልቁ ክርክር «ውሳኔ ላይ ብዙ ሰው ማሳተፍ» እና «ውሳኔን በፍጥነት መወሰን» እርስ በርሳቸው እንደሚጋጩ ማሳየት  ነው። ብዙ ሰው ሲሳተፍ ውሳኔው በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል፤ ሥራን በፍጥነት ለማስኬድ ግን የውሳኔ ሰጪዎችን ቁጥር መቀነስ ግድ ይላል። ይህንን ውጥረት መፍታት የምዕራፉ ዋና ጉዳይ ነው። 

ምዕራፍ ፩፦ የዜጎች ተሳትፎ፣ ፖለቲካዊ ተሳትፎ እና የምርጫ ሥርዓቶች