ምዕራፍ ፫፦ የዜጎች መብቶችና ግዴታዎች

ምዕራፍ ፪ ሥልጣን እንዴት እንደሚዋቀር መርምሯል። ይህ ምዕራፍ ግን ጥያቄውን ይገለብጠዋል፦ ዜጋው ለሥርዓቱ ምን ዕዳ አለበት፣ ሥርዓቱስ ለዜጋው ምን ዕዳ ... Show more
Instructor
CECOE
117 Students enrolled
0
0 reviews
  • Description
  • Curriculum
  • Reviews
1.jpg

ግቦች

ይህ ምዕራፍ የዜጋውን ሁለት ገጽታዎች — መብትና ግዴታ — በግለሰቦች፣ በማኅበረሰብና በመንግሥት መካከል ያለውን የዜግነት ትስስር ይፈትሻል፤ መብቶች ለዜጎች አቅም የሚፈጥሩበትን፣ ኃላፊነቶችም ለማኅበራዊ ኑሮ መሠረት የሚሆኑበትን መንገድ ያብራራል። 

በተጨማሪም ዜጎች መረጃዎችን በአግባቡ መዝነው በኃላፊነት እንዲሳተፉ እና የዲሞክራሲ ሥርዓታቸውን ከተዛቡ አመለካከቶች እንዲከላከሉ የወሳኝ አስተሳሰብ (critical thinking) ሚና ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ ያሳያል። 

 

ይህን ምዕራፍ ስታጠናቅቁ የሚከተሉትን ብቃቶች ታዳብራላችሁ፦

  1. የዜግነት ብቃት፦ ዜግነትን ከሕጋዊ እውቅና ባለፈ እንደ ንቁ ተሳትፎ የመረዳት፤ እና ሁለቱን የዜግነት ንድፈ-ሀሳቦች (ኖርማቲቭ እና ኢምፒሪካል) የመለየት።

  2. የመብትና ኃላፊነት ብቃት፦ የመብትና ኃላፊነትን እርስ በርስ መደጋገፍ (ተያያዥነት) የማብራራት፣ እንዲሁም የመብት ባለቤቶችን እና የግዴታ ተሸካሚዎችን የመለየት ችሎታ።

  3. የሰብአዊ መብት ብቃት፡ የሰብአዊ መብቶችን ትርጉም፣ መርሆዎቻቸውን እና ዋና ዋና ምድቦቻቸውን በተለይም የፖለቲካዊና የሲቪል መብቶች፣ የሶስዮ-ኢኮኖሚክ እና የባህላዊ መብቶች፣ እና የመደጋገፍ መብቶች የመለየት ብቃት ነው።

  1. ሕገ-መንግሥታዊ ብቃት፦  የዜግነት፣ የሰብአዊ መብቶች፣ የዴሞክራሲያዊ መብቶች እና ሃላፊነቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ከኢፌድሪ ሕገ-መንግስታዊ ማዕቀፍ እና ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መሳሪያዎች ጋር በማገናኘት የማብራራት እና የመተንተን ችሎታ ነው።

  2. የአስተሳሰብ ብቃት፦ ለጥልቀት አስተሳሰብ የሚያስፈልጉትን የአዕምሮ መመዘኛዎች እና መርሆዎች የመተግበር፤ የአመክንዮ ተግዳሮቶች እና እነዚህ ወሳኝ አስተሳሰብ በዜግነታዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳይ ምሳሌዎች ላይ ተግባራዊ ማድረግ

የማጠንጠኛ ሃሳብ፡ መብቶች ዜጎችን ከመንግስት እና ከማህበረሰብ ጋር ተያይዞ የሚያቀርቡትን ጥያቄ/መብት መሠረት ያላቸው የህጋዊ ጥያቄዎች ናቸው። ኃላፊነቶች ደግሞ ዜጎች ለሌሎች ሰዎችም ተመሳሳይ መብቶችን ማክበር እና ለጋራ መብት እና ጥቅም እንዲያበረክቱ ያግዛሉ። 

 

ነጻነት ያለ ኃላፊነት ሌሎችን ሊጎዳ ይችላል፣ እንዲሁም ሃላፊነት ያለ መብት ደግሞ “ዜግነት” ሳይሆን ትእዛዝ/መታዘዝ ብቻ እንደሆነ ሊቀየር ይችላል።

 

የዜጎች መብቶችና ግዴታዎች